ሐዋሪያዊ ተልዕኮ

ቤተ ክርስቲያናችን ትኩረት ሰጥታ ከምትሰራቸው ሥራዎች መካከል በዋናነት የሚጠቀሰው የወንጌል ተልዕኮ ሥራ ነው። የወንጌል ተልዕኮ ሥራችን የሚያካትተው ወንጌል ሥርጭት፤ ቤተ ክርስቲያን ተከላና ደቀ መዛሙርት ማድረግን ነው። እነዚህ ሦስቱም እርስ በርስ በመመጋገብ የሚሽን ሥራችንን ያሳልጡልናል።

በአሁኑ ሰዓትም 180 የሚያህሉ ሚሽነሪዎችን በመላው አገሪቱ ያሰማራን ሲሆን በዋናው ጽ/ቤት፤ በዞን ቢሮዎቻችንና በአጥቢያዎቻችን የወር ቀለብ ድጋፍ፤ የተለያዩ ሥልጠናዎች እንዲሁም ጉብኝትና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ።