መጋቢ ሳምሶን ወልደማሪያም

ምክትል ፕሬዝደንት እና የሥነ መለኮት ኮሌጅ ኃላፊ

መጋቢ ሳምሶን ወልደማሪያም ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ክልል በወለንጪቲ ከተማ ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለውም ከጥቅት 25 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በተነሳው የተሃድሶ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ መጋቢ ሳምሶን በተሃድሶ እንቅስቃሴው መሪ የነበረ ሲሆን በደ ጌታ የመጣው ተአምራተዊ በሆን መንገድ ነበር፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ሙሉ ጊዜውን በመስጠት በአማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ ከሌሎች ወንድሞች ጋር በመሆንም በዙ አጥቢያዎች በኢትዮጵያ ተክሏል፡፡

መጋቢ ሳምሶን በወለንጪቲ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በዋና መጋቢነት 1986 – 1996፥ ከ1997 – 2002 ደግሞ ወደ 3000 ምዕመናን ወዳሉት ናዝሬ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በመምጣት በዋና መጋቢነት ሲያገለግሎት ቆይቶ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በምክትል ፕሬዝዳንት እና በሥነ መለኮት ኮሌጅ ኃላፊ ሆኖ በማገልገል ላይ የገኛል፡፡ በብዙ የኢትዮጵያ ከቶሞችና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች በመጓዝ ለመሪዎች ወንጌል ላልደረሳችው መድረስ እንዲችሉ ስልጠናዎችንም ይሰጣል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የአገር ውስጥና አለም አቀፍ አገልግሎቶች ለምሳሌ አርክ ክርስቲያን ሰርቪስ እና ዩናይት ፎር አፍሪካ በምክትል ፕሬዝደንትና የቦርድ አባል በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

መጋቢ ሳምሶን የመጀመሪያ ዲግሪዎን ከአዲስ አበባ ፔንቴኮስታ ቲዮሎጂካል ኮሌጅ የተቀብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ናይሮቢ ኬኒያ በሚገኘው ፓን አፍሪካን ክርስቲያን ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪዎን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም ባለፈ መጋቢ ሳምሶን አስደናቂ ተናጋሪና ልብን በሚማርክ መልኩ የእግዚአብሔርን ቃል በመተረክ ይታወቃል፡፡ መሪዎችን ከማሰልጠን በተጨማሪ ለጌታችን እና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ይረዳ ዘንድ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን መሪዎች ለማሰልጠንና ለማስታጠቅ ከቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ጋር በመሆን የአማኑኤል ኅብረት ሥነ መለኮት ኮሌጅን በመመስረትና የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ በመሆንም እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ መጋቢ ሳምሶን ከወ/ሮ አዲስኪዳን ደርብ ጋር በጋብቻ ተጣምረው ሶስት ልጆችን በማፍራት የእግዚአበሔርን መንግስት በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች