የኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤ/ክ ጠቅላላ ጉባዔ

የኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤ/ክ የ2013 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባዔ ከመስከረም 5-7/2014 ድረስ በጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማዕከል ይካሄዳል፡፡

በነዚህ ቀናት የ 2013 አጠቃላይ የጽ/ቤቱ ሪፖርት ይደመጣል፤ እንዲሁም የ2014 ዓ.ም ዕቅድ ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርቦ ይጸድቃል፡፡ የአገልግሎት ጊዜያቸውን በጨረሱ የቦርድ አመራሮች ምትክ የቀጣይ አመራሮች ምርጫም ይካሄዳል፡፡ በተጨማሪም የቤተ እምነቷ ፕሬዝዳንት የአራት አመቱን ሪፖርት ያቀርቡና የመተመመኛ ድምጽ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
ከሁሉም አጥቢያዎች ያሉ መጋቢያንም እንደሚመጡ ይጠበቃል፡፡