የአዋቂዎችና የቤተሰብ አገልግሎት

የኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን ጤናማ ቤተሰብና ክርስቲያናዊ የአወቀቂዎች ሕይወት ወናዎቹ የእግዚአብሔር መንግስት አካላትና ለእግዝአብሔር መንግስት መስፋት ጉልህ ሚና እንዳለው በጽኑ ታምናለች፡፡ የአዋቁዎችና የቤተሰብ  አግልግሎትም አጥቢያዎች አገልግሎታቸውን በትጋት እንዲፈጽሙ  በትምህርትና ስልጠና በማጎልበትና የማስታጠቅ ኃላፊነት የተሰጠው ሲሆን በቤተሰብና ወደ ሙሉ ሰውነት ለማደግ በሚረዳ መልኩ ለሚደረግ አገልግሎት የሰራል፡፡ ያገቡም ይሁና ያላገቡ፥ ወጣቶች ይሁኑ ህፃናት፥ ወይም በመሃከል ላይ ያሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ  ሁሉንም ለመደገፍ እና ሁሉን አቀፍ ማኅበራዊ ሕይወት እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲኖራቸው እያገለገለች ትገኛለች፡፡

በአጥቢያዎችም በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ኅብረት በመታቀፍ የእግዚአብሔርን ዓላማና ክርስቲያናዊ ሕይወትን እለት ተእለት ለመለማመድ እያጠኑ እርስ በእርስም በሕይወት ስለሚገጥማቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎችና ስለ ተሻለ መንፈሳዊ እድገትና የቤተሰብ ኑሮ ይማማራሉ፡፡

Ministries and Departments