ሁለንተናዊ የልማት አገልግሎት

ቤተክርስቲያኒቱ ትኩረት ሰጥታ ከምታከናውናቸው ተግባራት መካከል፤ ሁለንተናዊ የልማት አገልግሎትን ነው፡፡ ስለዚህም የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በሚፈቅደው መሰረት የልማት ተግባራትን የሚያከናውን እራሱን የቻለ ተቋም፤ ማለትም ከመንግስት ፈቃድ ያለው፣ በራሱ ዳይሬክተር የሚመራ እና ቦርድ ያለው ተቋም በማቋቋም አጠቃላይ የልማት ሥራዎች በስፋት እየሠራች ትገኛለች፡፡ የልማት ማኀበሩ በዋናነት ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል፣ ከKHC፣ ከOCM እና ከመሳሰሉት አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በተለያዩ አጥቢያዎች ልጆችን እና አረጋውያንን ከመደገፍ በተጨማሪ አጥቢያዎች በራሳቸው አቅም የተለያዩ የልማት እና የሁለንተናዊ ሥራዎችን እንዲሠሩ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

በተጨማሪም አማኞች የሥራ ክቡርነትን ተረድተው እራሳቸውን ከተረጂነት አስተሳሰብ አላቀው፤ ለሀገራዊና ለሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ የሚበረታታ ነው፡፡ /ስለ ልማት ማኀበሩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለማግኘት በስተመጨረሻ የተቀመጠውን የልማት ማኀበር አድራሻ ይጠቀሙ፡፡

የአገልግሎት ዘርፍ ማስተባበሪያዎች