የቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪካዊ የተሃድሶ እንቅስቃሴ አጀማመር

የኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በ1980ዎቹ መጀመሪያ እውነተኛውን አምላክና የክርስቶስ አዳኝነት በመረዳት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስቲያን በተነሳ የተሃድሶ እሳት ስደት በገጠማው ወጣቶች አማካኝነት  የተተከለች ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡

ከደርግ የኮሚዩኒስት ስረዓት ከወደቀ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች በብዙ ለእግዝአብሔር ካላቸው ረሃብና መሰጠት ጋር በብዙ ቁጥር መመለሳቸው የሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲጠናከሩና በየእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርኃ ግብሮች እንዲከወኑ ከፈተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ ከዚህም የተነሳ ፅዋ ማኅበር የተባለ ማኅበር መመሥረት ችሏል፡፡

በእነዚህ ማኅበራት መዳን እንዴት እንደሚቻል፥ ስለ ኢየሱስ እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች መነሳት ጀመሩ፡፡ እነዚህ መሠረታዊ ጉዳዮች በቀዳሚነት የመወያያ ጉዳዮቻችንና ከመሆን ባለፈ የቤተ ክርስቲያኒቱን  አስተምህሮ ከቀሳውስቱ የሕይወት ዘይቤ ጋር ተዳምሮ ጠያቂዎችና አድርጎን ነበር፡፡ እንዚህ ምክኒያቶችና ሁኔታዎች የተሃድሶ ጅማሬዎች ሆነዋል፡፡

በስተመጨረሻም እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ የማዳኑን እውቀት ያበራልን ጀመረ፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር የሩቅ አምላክ እንዳልሆነ ተረዳን፤ የአለም መድሃኒት ብቻ ሳይሆን የእኛም አዳኝ እንደሆነ ስሙን መጥራ ጀመርን፡፡ የክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ሳይሆን የሕይወታችን ዘይቤ መሆን ጀመረ፡፡ በዚህ አዲስ ፍጥረት የመሆን ልምምድ መደነቅ ጀመርን፡፡ በመልእክቱም ይሁን በዜማውም አዳዲስ ዝማሬዎችን መዘመር ይህም ወደ እግዚአብሔር ይበልጡኑ ያቀርቡን ጀመረ፡፡ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ ልባችን እለት ከእለት ሃሴት ያደርግ ጀመረ፡፡

ሁላችንም ተነስተን ይህን የምስራቹን ወንጌል በቤተ ክርስቲያኒቱ ሰንበት ትምህረት ቤት መስበክ ጀመርን፡፡ እነዚህ ነገሮች ግን በቤተ ክርስቲያኒቱ ባለ ስልጣናት አልተወደደም ነበር፤ ከተነሳው የተሃድሶ እንቅስቃሴ የተነሳ መፍራትም በመጀመራቸው በገሃድ ስደትና ማግለል በቤተ ክርስቲያኒቱ ተነሳብን፡፡

በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሰው ይህ የተሃድሶ እንቅስቃሴ በአንድነት በማበር ናዝሬት ከተማ (አዳማ) ውስጥ በናዝሬት የተሃድሶ እንቅስቃሴ ማኅበር መሪነት  የኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን እንዲመሠረት አስችሎታል፡፡

በብዙ ስደት፥ መከራ እና ፈተናዎች እየለፈንና አዳዲስ የተሃድሶ ማኅበራት አየተጨመሩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት በ በአገሪቱ ውስጥ የተተከሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ወደ 680 አጥቢያዎችና 554 000 የሚጠጉ የክርስቶስ ደቀመዝሙርቶችን ማፍራት ችለናል፡፡ እነዚህ ምክኒያቶች ለኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ከርስቲያን መስፋትና እደገት ምክኒያት ሆኗል፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱ