የወጣቶች፥ ሴቶችና ሕፃናት

በኢትዮጵያ ውስጥ ሰባ ከመቶ የሚሆነው ትልቁ የሕዝብ ድርሻ ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወጣቱን ትውልድ የሚገዳደሩ ከቁጥር በላይ ተግዳሮቶች በመኖራቸው ምክኒያት ቤተ ክርስቲያኒቱ የወጣቶች፥ የሴቶችና ህፃናት አገልግሎት በጣም አስፈላጊ መሆንን ትረዳለች፡፡ ስለዚሀም የወጣቶች፥ ሴቶችና ህፃናት አገልግሎትም ለእግዚአብሔር መንግስት ባለ አደራዎች በመኮትኮትና በማስታጠቅ በትጋት የሚሰራ የአገልግሎት ክፍል ነው፡፡

የወጣቶች፥ ሴቶችና ህፃናት አገልግሎትም ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት አገልግሎቱን በመምራ፥ በመከታተል፥ በመደገፍና የአገልግሎቱን መበልፀጊያ እቅድ በማዘጋጀት ያግዛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አጥቢያዎችን አገልግሎት በተለያየ መንገድ በማሰልጠን፥ በቦታው እየተገኙ በመከታተልና ተጨማሪ ድጋፎችን በማድረግ ያግዛል፡፡

የሴቶችም ድርሻ ከወጣቶቹ አስተዋፅኦ ባልተናነሰ ከፈተኛ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሴቶችም ለእግዚአብሔር መንግስት ሥራ ከፍተኛ አስተዋፆኦ እንደሚያበረክቱ ስለምታምን እንደ ተሰጣቸው ፀጋ መጠንም  ፍሬያማ እንዲሆኑ በመሥራት ላይ ትገኛለች፡፡ የህፃናት አገልግሎትም ዋና ጉዳይ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቱ አበክራ በመሥራት ላይ ተገኛለች፡፡ በአጠቃላይ አገልግሎቱ ከአጥቢያዎች ጋር በመሆን ወጣቶች፥ ሴቶችና ህፃናት በተሰጣቸው የእግዚአብሔር ፀጋ መጠን ፍሬያማ እንዲሆኑ በመምራት፥ በመከታተልና በማገዝ ያገለግላል፡፡

የአገልግሎት ዘርፎችና ማስተባበሪያዎች