የቤተእምነቷ አስቸኳይ እገዛ እና ትብብር የምትሻባቸው የአገልግሎት ዘርፎች

የኢትዮጵያ አማኑኤል ኀብረት ቤተክርስቲያን በዋናነት በሚሽን ሥራ ላይ ከፍተኛ እገዛን ትሻለች፡፡ በተለይ በገጠር አካባቢ ሚስዮናዊያንን በስፋት ለማሰማራት እና ቤተክርስቲያን ለመትከል ያላትን እቅድ ለማሳካ አፋጣኝ የሆነ እገዛን ትሻለች፡፡ ለዚህም ወጪ የመጋራት ስልቶችን በመንደፍ ለአንድ ሚስዮናዊ ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያን ታሣቢ በማድረግ ብር 2000 ከድጋፍ ሰጪ አካላት በማፈላለግ እና ቤተእምነቷ ደግሞ ተጨማሪ ብር 1000 ጭማሪ በማድረግ የብር 3000 ክፍያ በመፈጸም የሚሽኑንን ሥራ በስፋት ለመሥራት አቅጣጫዎችን አስቀምጣለች፡፡ ስለሆነም ከአንድ ሚስዮናዊ ጀምሮ ግለሰቦች እና አጋር ድርጅቶች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ከጎኗ እንዲቆሙ ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡

በትምህርት እና ስልጠና እንዲሁም በከፍተኛ የስነ መለኮት ኮሌጅ ደረጃ ሸክሙ ያላቸው እና አብረዋት በአጋርነት ለመሥራት ለሚሹ ግለሰቦች እና መንፈሳዊ ድርጅቶች ቤተእምነቷ በሯ ክፍት ነው፡፡ በተለይ በአጭር እና በረጅም ጊዜ ስልጠና መሪዎችን እና አገልጋዮችን በማስታጠቅ ላይ የሚያግዙ አካላት ቅድሚያ በመስጠት እና የወጪ መጋራት ስልቶችን ጭምር በማዘጋጀት በእድሉ ለመጠቀም ትሠራለች፡፡

የኢትዮጵያ አማኑኤል ኀብረት ቤተክርስቲያን ገና የአንድ ወጣት እድሜ ላይ ያለች ቤተእምነት እንደመሆኗ በዚህ ዘርፍ በርካታ ሥራዎችን አልሠራችም፡፡ ክፍሉን እንኳ ራሱን በቻለ መንገድ የሚያስተባብረው ሰው ማዘጋጀት የተቻለው በቅርብ ጊዜ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ዘርፍ ስልጠናዎችን፣ ለስልጠና የሚያግዙ ማቴርያሎችን እና ተመሳሳይ የሆኑ እገዛዎችን በእጅጉ ስለምትሻ ሸክሙ ያላቸው አካላት አብረው እንዲሠሩ በፍቅር ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡

የኢትዮጵያ አማኑኤል ኀብረት ቤተክርስቲያን አገር በቀል ተቋም መሆኗና ገቢዋ ከአጥቢያዎች የሚሰበሰብ የፈሰስ ክፍያ ብቻ በመሆኑ፤ ራዕይዋን በሚፈለገው ፍጥነት እንዳታሮጥ እንቅፋት ፈጥሮባታል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በአገር ውስጥ እና ከቅርብ ጊዜ ወድህ ደግሞ በውጭ አገራትም የታላቁ ተልእኮን ግብ ለማሳካት የምታደርገው ጥረት ከፍተኛ ቢሆንም፤ እስከ አሁን ድረስ የራሷ የሆነ ቦታ የላትም፡፡ በቅርቡ ከመንግሥት የተረከበችው ቦታ ቢኖርም፤ በቦታው ላይ ቦታው በሚጠይቀው ልኬኬ ለመገንባት የአቅም ውስንነት አለባት፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ ከፍ ያለው እገዛ ትሻለች፡፡

በተጨማሪም ሰፊውን አገልግሎቷን ለማሳለጥ የመስክ መኪኖች፣ የቢሮ ኮምፒተሮች እና ተያያዥነት ያላቸው መርጃ መሳሪያዎች ቤተእምነቷ በእጅጉ የምትሻቸ ነገሮች ስለሆኑ በዚህ በኩል ያለባትን ክፍተት የሚሞሉ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን በፍቅር ትጋብዛለች፡፡

ለእገዛ እና ትብብር

የኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን

ንግድ ባንክ
Ac. No:1000000921207
Swift: CBETATA

ብርሃን ባንክ
Ac. No: 2500090019823
Swift: